ለነባርና አዲስ የኮንስትራክሽን (BC/GC)ፍቃድ ተመዝጋቢዎች በሙሉ

 ለነባርና አዲስ የኮንስትራክሽን (BC/GC)ፍቃድ ተመዝጋቢዎች በሙሉ
ከዚህ በታች በሰፈረው አዲስ የተርን ኦቨር ባለሙያና የኮንስትራክሽን መሳርያዎች መስፈርት መሰረት በማሟላት ፈቃድ ማግኘት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከተጠቀሰው መስፈርት ዉጭ የሚመጣ ማንኛዉም ደንበኛ የማናስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ 

ለእድሳትም ሆነ አዲስ ብቃት ማረጋገጫ ለማውጣት ሲመጡ ለሚፈልጉት ደረጃ ማንኛውም ማስረጃዎች ኦሪጅናላቸውን ከ2 ኮፒ ጋር አያይዘው እንዲቀርቡ ከወዲሁ እያሳሰብን ማስረጃዎቹም፤-
 የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ የፕራክቲሲንግ ፕሮፌሽናል የምስክር ወረቀት/ላይሰንስ ሊኖረው ይገባል ካልሆነ ከተቆጣጣሪ ማሃንዲሱ ጋር በድርጅቱ ስራ አስኪያጅነት የተዋዋለበትን ማስረጃ ማቅረብ አለበት
 ለስራ ዘመኑ ዓመታዊ ተርን ኦቨር የሚያሳይ ማስረጃ፤የተሸከርካሪ ምርመራ (ዕድሳት)የተደረገለት መኪና ሊብሬ፤ለስራ ዘመኑ የሚያገለግል(የታደሰ) የባለሙያ ፕሮፌሽናል ላይሰንስ፤ህጋዊ የስራ ዉል፤ቲን ነምበር(የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት)፤የባለሙያው የትምህርት ዶክመንት፤ባለሙያው ቀድሞ ሲሰራበት ከነበረው ድርጅት ስድስት ወር ያላለፈው የስራ መልቀቂያ፤የቀበሌ መታወቂያ…….. እና ሌሎችም ሲሆኑ ከዚህ ዉጪ የሚመጣ ደንበኛ የማናስተናግድ መሆኑ እንገልጻለን፡፡