ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም በአዋሽ ሰባህ ኪሎ ከተማ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የህዝብ መሠብሰብያ አዳራሽ ጎበኙ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም በአዋሽ ሰባህ ኪሎ ከተማ ላይ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ደረጃውን የጠበቀ የህዝብ መሠብሰብያ አዳራሽ የግንባታ ሂደትና በአዋሽ ከተማ በ2014 ዓመቱ ውስጥ በUiidp የከተማ መሠረተ ልማት ማስፋፍያ ፕሮግራም የተጀመሩት የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ስራዎች አፈፃፀማቸውን ምን እንደሚመስሉ ስራዎቹ በሚከናወኑባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት የስራ ጉብኚት አካሄዱ። በስራ ጉብኚቱ ላይ በአዋሽ ከተማ በመገንባት ላይ ያለው ደረጃውን የጠበቀ የህዝብ መሰብሰብያ አዳራሽ የግንባታ ሁኔታ 60% የደረሰ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ቀሪውን በመገንባት ላይ ያለው የመሰብሰብያ አዳራሽ ግንባታና በUiidp የከተማ መሠረተ ልማት ማስፋፍያ ፕሮግራም በከተማው በመገንባት የተጀመሩ ኘሮጀክቶች\ ደካማ አፈፃፀም ያላቸውን አፈፃፀማቸውን በማሻሽል በተያዘላቸው ጊዜገደብ ተጠናቀው ለተፈለገለት ዓላማ መዋል እንዳለባቸው በመጠቆም ለቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ላይም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።