የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና ከአዲስ አበባ ስካይሊንክ ቴክኖሎጂ የመጣ ቡድን ጋር

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮና ከአዲስ አበባ ስካይሊንክ ቴክኖሎጂ የመጣ ቡድን ጋር በጋራ በመሆን አጠቃላይ በሶፍትዌር የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥና የመከታተል ስርዓት ዝርጋታ ዙርያና የቢሮው ዌብሳይቶች በመጠቀም መረጃን ለህብረተሰቡ ተደረሽ ለማድረግ ከቢሮው የማኔጅመንት አባላትና የክልሉ Uiidp ፕሮግራም ሞባይል ቲም ጋር ውይይት አካሄዱ። በመቀጠልም በውይይቱ በቀረበው አጀንዳ ላይ ማለትም የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥና መከታተል ስርዓት የቢሮው ዌብ ሳይቶችን በተሻሻለ ደረጃ ለማዘመን መደረግ በሚገባቸው ላይ በስፋት የተወያዩበት ሲሆን በስተመጨረሻም ለቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ላይም የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።