በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ የተከበሩ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም ለ2017 አዲሱን ዓመት ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መልእክት።
2017 አዲሱ ዓመት ተስፋን ሰንቆ የሚመጣ ዓመት እንደመሆኑ መጠን የጀመርናቸው የከተማ መሰረተ ልማት ስራዎቻችን በማሳለጥና አጠናክረን በመቀጠል ከተሞቻችንና እኛነታቻችን ጋር በጋራ አብረን የሚንበለፅግበት ዓመት እንዲሆንልንና በኢኮኖሚ የዳበረ፣ ውብና ጽዱ ከተሞችን በመፍጠር ለትውልድ የምናወርስበት ዓመት እንዲሆንና አዲሱ ዓመትም ለሚተገበሩና ለሚከናወኑ ስራዎች ከነበሩበት ደረጃ የበለጠይ ስራዎችን በማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ፣ የስራ ዕድል ፈጠራን በማጠናከር ፣ የከተሞች መሰረተ ልማት ዝርጋታ በተገቢው ሁኔታ በማሳለጥ ፣ ከተሞቻችን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ እንድሆኑ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት ሽፋኖችንን በማሳደግ ፣የከተሞች የገቢ አቅም ማሳደግና የከተሞች ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት አድርገን ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ በመስራት ስኬታማ እንድንሆን በቁርጠኚነት ስራዎችን አጠናክረን የምንሰራ እንዲሆን እንዲሁም እኛነታችንና ስራዎቻችን ከነበርንበት ወደ ተሻለ ከፍታ ማማ ላይ የምንደርስበት ዘመን እንዲሆንልን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስራዎቻችንን በአንድነት አጠናክረን የምንበለፅግበት ዘመን እንዲሆንልን ለማለት እወዳለሁ በማለት የቢሮው ሀላፊ የተከበሩ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም መልካም ምኞታቸውን የገለፁ ሲሆን በአዲሱ ዓመት ከጦርነት፣ ከጥላቻ መንፈስ፣ ከዘረኚነትና ከጎጠኚነት ወጥተን በጋራ ተደጋግፈን ተግተን በመስራት ከራሳችን አልፈን ለማህበረሰባችንና እንዲሁም አልፎም ለሀገራችን የምንጠቅምና የሰላምን አየር በመተንፈስ መልካም የሆኑ ነገሮችን የምናጣጥምበት ዓመት ይሁንልን በማለት የመልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።🇪🇹
🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት🌻
🇪🇹ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም 🌻
🇪🇹በአፋር ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ 🌻