የ2015 በጀት ዓመቱ እቅድና ለቀጣይ የ10 ና 5 ዓመቱ
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2015 በጀት ዓመቱ እቅድና ለቀጣይ የ10 ና 5 ዓመቱ ማለትም (2013-2022) ድረስ ሊተገበሩ በታሰቡ መሪ እቅድ (Strategih Plan) በማስመልከት ከቢሮው የማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ። በመቀጠልም በቀረቡት የ2015 በጀት ዓመቱ እቅድና የ10 እና 5 ዓመቱ ሊተገበሩ በታሰቡ መሪ እቅድ (Strategi Plan) ላይ መሻሻል በሚገባቸው ላይ በማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና ጉዳዬች ላይ በስፋት የተወያዩባቸው ሲሆን በውይይቱ መጨረሻ ላይም ለቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ላይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።