በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2013 በጀት ዓመቱ ዕቅድ የስራ አፈፃፀም ምን ይመስል እንደ ነበር እና የ2014 በጀት ዓመቱ ላይ ሊተገበሩ የታሰቡ ዕቅዶች ምን እንደሚመስሉ አጠቃላይ ከሴክተር መስሪያ ቤቱን ሠራተኞችን ጋር ውይይት አካሄዱ።በውይይቱ መድረክ ላይም በ2013 በጀት ዓመቱ ላይ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀማቸው ደካማና ጠንካራ የሆኑትን በመገምገም የታዩ ሲሆን በታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና በታዩ ክፍተቶችና ችግሮችን በመቅረፍ ስራዎች ማስቀጠል ይጠበቅብናል በማለት የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም በ2014 በጀት ዓመቱ እቅድ ትግበራ ላይ ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው ዋና ዋናዎቹ -
1. የቢሮው የውስጥ ኦዲትን ማጠናከር።
2. የቢሮው የውስጥ ገቢ ማጠናከር።
3. የአፋር ልማት ማህበርን ማጠናከር።
4. የቢሮው ኮሚኒኬሽን ጉዳዬችን ማጠናከር።
5. በቢሮው የድርጅት አባላትን ማጠናከር።
6. በክልሉ ደረጃ በUiidp ፕሮግራም የማሠሩ የከተማ መሠረተ ልማት ስራዎችን ማጠናከርና
7. የስራ ዕድል ፈጠራን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልፀዋል።
በስተመጨረሻም በሴክተር መስሪያ ቤቱ ደረጃ በሚከናወኑና በሚተገበሩ ስራዎች ሀላፊነትን አመራሩ ላይ ብቻ መተው ሳይሆን ሁሉም እንደየ ስራ ድርሻው ሀላፊነት በመውሰድ ቢሮው በ2014 በጀት ዓመቱ ላይ ሊተገበሩ ባቀደው ዕቅድ መሠረት አጠቃላይ የሴክተር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ወቅቱን ጠብቆ በመተግበርና ሁሉም የሴክተር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ በወቅቱ በመገኘት የተሰጣቸውን የስራ ድርሻ በአግባቡ መወጣት ይጠበቅባቸዋል በማለት የቢሮ ሀላፊው ከአደራም ጭምር አሳስበዋል።