የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር
በሀገር አቀፍ ደረጃ በያዝነው የአምስተኛው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ ዘንድሮ በጋራ ለምንተክለው 6.5 ቢልዮን በላይ የሚሆን ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝግጅት በመካሄድ ላይ መሆን ይታወቃል። በዛሬው ዕለት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በበኩሉ ለሚካሄደው የችግኚ ተከላ መርሀ ግብር ቅድመ ዝግጅት በማካሄድ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑና የቢሮው ከፍተኛ አመራሩና የቢሮው የማናጅመንት አባላት በጋራ በመሆን በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት አከባቢ በሚገኘው አደባባይና አከባቢው ላይ ሳር የመዝራትና የአረንጓዴ ልማትና የችግኚ ተካላ ስራ በመጀመር የችግኚ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል።