በሰመራ ሎግየ ከተማ ነባር የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥብ Ground Control Point (GCP) ጥበቃ ማድረግ እና በከተማዉ ተጨማሪ የቅየሳ መቆጣጠሪ ነጥቦችን ማስፋፋትና እና ማብዛት
በሰመራ ሎግየ ከተማ ነባር የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥብ Ground Control Point (GCP) ጥበቃ ማድረግ እና በከተማዉ ተጨማሪ
የቅየሳ መቆጣጠሪ ነጥቦችን
ማስፋፋትና እና ማብዛት ላይ የክልሉ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ ክልሉ ፕላን ኢንስቲትዩት እንዲሁም የሰመራ ሎግያ የከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በሰመራ ከተማ በግልፅ የሚታዩ የፕላን ጥሰቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም የከተማዋ ፕላን ተጠብቆ እንዲቀጥል የሚያስችል ስራ በወኔ እና በቁርጠኝነት ወደ መሬት አውርደው መስራት ከተጀመረ ሰንበት ብሏል .. የከተማዋን የቅየሳ መቆጣጠርያ ነጥቦችን GCP በግልፅ በማስቀመጥ እና ከመቆጣጠሪያ ነጥቦች በመነሳት ከፕላን ውጭ የሆኑ የፕላን ጥሰቶች የፈፀሙ ህገወጥ ፕላኖችን ለይቶ የማስቀመጥ እንዲሁም በቅርብ ጊዜያቶች በነዚሁ የፕላን ጥሰት በፈፀሙት ላይ ስርዓት የማስያዝ ስራ እንደሚሰራ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም ገልፀዋል። በመጨመርም ከዚህ በፊት በነበሩት ግዜያቶች የተፈፀሙ የፕላን ጥሰቶችን በማስተካከል ላይ ተጠምደን በፈለግነው ፍጥነት እንዳንራመድ ሲጎትተን እንደነበረ የሚታወቅ ነው።
'' ዘመናዊ ከተማ የሰለጠነ ህዝብ መለያ ነው'