የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም በአሳይታና ዱብቲ የስራ ጉብኚት አካሄዱ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም በአሳይታና ዱብቲ በሁለቱ የከተማ አስተዳደር በUiidp የከተሞች መሠረተ ልማት ማስፋፍያ ፕሮግራም የተጀመሩትን የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ስራዎች አፈፃፀማቸውን ምን እንደሚመስል ስራዎቹ በሚከናወኑባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት የስራ ጉብኚት አካሄዱ። በስራ ጉብኚቱ ላይም የተጀመሩ ኘሮጀክቶች ደካማ አፈፃፀም ያላቸውን አፈፃፀማቸውን በማሻሽል በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለተፈለገለት ዓላማ እንዲውሉና ለህብረተሰቡ ክፍት ሆነው ግልጋሎት እንዲሰጡ መሆን እንዳለበት በመጠቆም ለቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ላይም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።