.በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በተቀናጀ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ጉዳዬች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሰጥ ባቀደውና በጠየቀው መሠረት የፌዴራል ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ በተቀናጀ ልዩ ድጋፍ በሚሹ ጉዳዬች ላይ 40 ለሚሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትና ባለሙያዎች ለ3 ቀናት ያክል የአቅም ግንባታ ስልጠና በሠመራ ከተማ በመስጠት ላይ ይገኛል። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮሀላፊ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም ሲሆኑ እሳቸው እንዳሉትም ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና ስልጠናው በሚሰጥባቸው ጉዳዬችና በዘርፎች ላይ በስራዎች ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ሊቀርፍና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ስልጠና ከመሆኑም አንፃር ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡና ሳያቋርጡ በፅሞና ሊከታተሉት ይገባል በማለት ለሰልጣኞች ከአደራም ጭምር ገልፀዋል። የአቅም ግንባታ ስልጠናውን የተካፈሉና የተሳተፉ አካላትም ከቢሮው ደረጃ የሚገኙ ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ከአይሳኢታ፣ ከዱብቲ፣ ከአዋሽ፣ ከሎጊያ ሰመራ የከተማ አስተዳደርና ከማዘጋጃ ቤቶች የተውጣጡና የመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ናቸው። የስልጠናው ዋነኛ አጀንዳም
>በከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት፣
>በከተሞች ፕላን ዝግጅት ትግበራና ክትትል፣
>በከተሞች የአየር ለውጥ ተፅእኖ ማቋቋሚያ፣
>በከተሞች መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ፣ >በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰራርና ማሻሻያ ሰነዶች ዙርያ ላይ ሲሆን ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት የስልጠናና የአቅም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሰፋ ባለ መልኩ ይወያያሉ።