በፌዴራል የከተማ መሰረተ ልማት ሚኒስተር ዴዕታ ክብርት ሄለን ደበበ የሚመራው የከተማ እና መሰረተ ልማት የክትትልና ቁጥጥር ቡድን በክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2017 በበጀት ዓመቱ በ6ወር አፈፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ አካሄዱ።
በፌዴራል የከተማ መሰረተ ልማት ሚኒስተር ዴዕታ ክብርት ሄለን ደበበ የሚመራው የከተማ እና መሰረተ ልማት የክትትልና ቁጥጥር ቡድን በክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በ2017 በበጀት ዓመቱ በ6ወር አፈፃፀም ምን እንደሚመስልና አጠቃላይ በሴክተር መስርያ ቤቱ ደረጃ የተከናወኑ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ከቢሮው አመራሮች፣ ከሰመራ ሎጊያ የከተማ አስተዳደር አመራሮችና እንዲሁም የማናጅመንት አባላቱና ሰራተኛች ጋር የአፈፃፀም ግምገማና የውይይት መድረክ አካሄዱ።
በመቀጠልም በቀረበው የ2017 በጀት ዓመቱ የ6ወር አፈፃፀም ጠንካና ደካማዎቹ ምን እንደሆኑና የታዩ ክፍተቶች የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲሁም በውይይት መድረኩ ላይ በተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ ምላሾችን በመስጠት ሰፋ ባለ መልኩ ተወያይተዋል።
በመቀጠልም የተለያዩ የከተማ መሰረተ ልማት ስራዎችን ምልከታና የስራ ጉብኚት ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።