የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ስራዎችን በማስመልከት የአቅም ግንባታ ስልጠናና የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል

በፌዴራል የከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ማሻሻያና ፈንድ ሞባላይዜሽን ቢሮ እና በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በጋራ በመተባበር በክልሉ ደረጃ በUiidp ፕሮግራም በመከናወንና በመከናወን ላይ የሚገኙ የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ስራዎችን በማስመልከት የአቅም ግንባታ ስልጠናና የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በውይይት መድረኩ ላይም በክልሉ በUiidp የታቀፉ 4ቱ የከተማ አስተዳደሮች ደረጃ በ2014 በጀት ዓመቱ በ9 ወራት ውስጥ የተከናወኑ የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ማስፋፍያ ስራዎችን በማስመልከት ሪፓርት የቀረበ ሲሆን በውይይት መድረኩ ላይ በቀረበው ሪፖርት ላይም በስፋት በመወያየት የታዩ ክፍተቶች መሻሻል በሚገባቸው ላይ በማሻሻል ለቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ላይም የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።