ከከተማ ልማት ከሰመራ ከተማ አስተዳደር እና ከኮንሰልታንት ተወጣጥቶ የልምድ ልውውጥ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተከናወኑ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮርደር ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታና የስራ ጉብኚት አካሄዱ።
በኢ ፌዲሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት የሰመራን ኮሪደር ልማት ከሚያግዙ በአዲስ አበባ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ከሚመራ የኮሪደር ልማት አስፈፃሚ አካላት ጋር በዛሬው እለት ከከተማ ልማት ከሰመራ ከተማ አስተዳደር እና ከኮንሰልታንት ተወጣጥቶ የልምድ ልውውጥ ለመውሰድ ወደ አዲስ አበባ የሄደው የልዑካን ቡድን በጋራ በመሆን ልምድ በመቅሰም እና የኮሪደር ልማት ስራዉን ወደ ሰመራ ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የልምድ ልውውጥ የኮሪደር ልማት አስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
በመቀጠል ከውይይቱ በኋላም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተከናወኑ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮርደር ልማት ስራዎችን የመስክ ምልከታና የስራ ጉብኚት አካሄዱ።