የ2016 በጀት ዓመቱ ሊከናወኑ የታሰቡ ስራዎችና ቢሮው ሊያከናውናቸው ባቀደው እቅድ
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2016 በጀት ዓመቱ ሊከናወኑ የታሰቡ ስራዎችና ቢሮው ሊያከናውናቸው ባቀደው እቅድ ላይ ቅድመ በጀት ፍላጎት ከቢሮው የማናጅመንት አባላት ጋር ተወያዩ። በመቀጠልም በቅድመ በጀት ፍላጎት ላይ መካተት በሚገባቸውና መሻሻል በሚገባቸው ላይ በስፋት የተወያዩ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችም አስቀምጠዋል።