በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር
የክልሉ መንግስትና የብልፅግና ፓርቲ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት መነሻ በማድረግ በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር ላይ የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በያሎ ወረዳ ማዕከል ላይ ለአቅመ ደካማ ቤት ያስገነባ ሲሆን የተገነባው ቤት ግንባታውን በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት የቢሮው ሀላፊ ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም የዞንና የወረዳው አመራርሮች እንዲሁም የቢሮው ማናጅመንት አባላትና የወረዳው ህብረተሰብ በተገኙበት የምረቃ ስነ-ስርዓት አካሄዱ።
በመቀጠልም የተገነባውን ቤት በማስመረቅ የተገነባውን ቤት ከቢሮ ሀላፊው ኢንጅነር አህመድ ኑር ሳሊም እጅ በወረዳው የሚገኙት አቅመ ደካማ የለሆኑት ለወ/ሮ አባሂና ሚስባህ የቤቱን ቁልፍ አስረክበዋል።
በመቀጠልም ከመረሀ ግብሩ ጎን ለጎን የቢሮው ሀላፊ እና የማናጅመን አባላቱ እንዲሁም የወረዳና ዞን አመራሮች ወረዳ የተለያዩ የመሰረተ ልማትና የመስክ ስራዎችን ጎብኚተዋል።