በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በድጂታል ዘርፍ በክልሉ ግንባር ቀደምና ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይታወቃል።


በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በድጂታል ዘርፍ በክልሉ ግንባር ቀደምና ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይታወቃል።
ቢሮውም የስራና አሰራር ስርዓቱን ወደ ድጅታል መቀየር ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ የአይሲቲ ማዕከል በመገንባት የ2025 ድጅታል ኢትዮጵያን ራዕይን እውን ለማድረግ አንግቦና በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኚ ቢሮ ነው። 

የዚህም አካል የሆነው በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተጀመረው የ5 ሚልዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ መነሻ በማድረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራር እንዲሁም ሰራተኞች በዚህ ፕሮግራም እየተሳተፉ ይገኛሉ። 
ቢሮው በድጅታል የተዋቀረ በመሆኑና ዘመናዊ አይሲቲ ማዕከል መኖሩ ለዚሁ ኢኒሼቲቭ አጋዥ ሁኗል።

እስካሁን 41 ሰዎች ኮርሱን ያገባደዱ ሲሆን  43 ሰዎች ደግሞ በሂደት ላይ ይገኛሉ።
በቀጣይ ለከተሞችና ለሴክተር መስርያቤቶች ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁን ጨርሷል።