የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በሰመራ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተሰሩና የተጀመሩ እንዲሁም ሊሰሩ የታሰቡ የአረንጓዴ ልማት ፓርክ ዲዛይኖች
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
በሰመራ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተሰሩና የተጀመሩ እንዲሁም ሊሰሩ የታሰቡ የአረንጓዴ ልማት ፓርክ ዲዛይኖች ዙርያ ላይ ከአፋር ክልል ዲዛይንና ቁጥጥር እንዲሁም ከክልሉ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከቢሮው ማናጅመንት አካላትና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄዱ።
በመቀጠልም በቀረበው የአረንጓዴ ልማት ፓርክ ላይ መጨመር መቀነስና መስተካከል እንዲሁም መሻሻል አለበት በሚለው ላይ ሰፋ ባለ መልኩ የተወያዩበት ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።