የፕላስቲክ ሃይላንድ ጎማዎች ፈጭቶ Recycle የሚያደርግ ማሽን ርክክብ
በዛሬው እለት 26/07/2016 ዓ.ም በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አካባቢን እየበከለ የሚገኘውን የፕላስቲክ ሃይላንድ ጎማዎች ፈጭቶ Recycle የሚያደርግ ማሽን በ700,000 ብር አስመጥቶ ለሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ለሚገኙ ጥቃቅን እና አነስተኛ ወጣት ማህበራት የማስረከው ስራ ተካሄደ። በርክክቡ ወቅት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አህመድ ኑር ሳሊም የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በተገኙበት ርክክብ ተደረገ።
በርክክብ ወቅቱም NN Recycling ከተባለ ካምፓኒ ጋር የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር ተገልፆዋል።