የ2018 ዓ.ም በሰመራ ከተማ ለሚካሄደው 10ኛው የከተሞች ፎረም ቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ።

ሰመራ (SEMERA)፡  የ2018 ዓ.ም 10ኛው  የከተሞች ፎረም የሚከናወንበት ከተማ፡

በ2016 ዓ.ም  በወላይታ ሶዶ የተካሄደው  9ኛው የከተሞች ፎረም ከ120 ከተሞች ባላይ ተሳትፋው፤ የሠሩትን ሥራ፣ ልማት ተወዳዳሪነታቸውን በሚደንቅ መልኩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሳዩበት እንዲሁም  ከተሞች ለሀገር ልማት የመሪነት ሚናቸውን እንደሚጫውቱ ያሳዩበት የሚያስደምም መድረክ ነበር፡፡ እርግጥ ነው ያለ ከተሜነት እና ከተማ ያደገ አገር የለም፡፡ ከተሜነት እና ኢኮኖሚክ ልማት የማይነጣጠሉ እና ጥብቅ ዝምድና ያላቸው ናቸው፡፡

አሁን ደግሞ የ10ኛውን የከተሞች ፎረም ዝግጅት በሰመራ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ የሆነችው -ሰመራ እንግዶቿን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት ለማድረግ ደፈ ቀና ማለት ጀምራለች፡፡ ይህንም የአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት የከተማ እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃለፊ ኢንጂነር አህመድ ኑር ከሰመራ ከንቲባ እና ከክልሉ ከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጋር በመሆን ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ጀምሯል፡፡ እኔም ሙያዊ ድጋፍ በሚሰጥበት ተገቢውን እያበረከትኩ ነው፡፡ ዘሬ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ዝግጅቱ ትኩረት ሊደረጉ የሚገቡ ጉዳዮች ቦታ መነረጣን ጨምሮ እንዲሁም ከ10ኛው ከተሞች ፎረም ምን ምን ፀጋዎች እና ቱሩፋቶች ይገኛሉ በሚሉ ሐሳቦች ጥልቅ ውይይቶች ተደርጓል፡፡ እኔም የመነሻ ሐሳብ አቅርቤዋለሁ፡፡

ኢንጂነር አህመድ ኑር የክልሉ የከተማ እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ እየደየረጉት ያለው እንቅስቃሴ ራዕይ ከላቸው (INSPIRATIONAL AND TRANSFORMATIONAL LEADERS) መሪዎች የሚጠበቅ ነው፡፡ አጠናክረው ይቀጥሉ እላላሁ፡፡

ሠመረ የአገራችን የገቢ-ወጪ ኮሪደር ናት፤ ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚታገናኝ ናት፡፡ የደረቅ ወደብ ተጠናክሮ የሚደረጅበት ሥፍራ ነች፡፡ ሠመረ ውብ እና ፅዱ እንዲሁም (ECO-CITY) አሮንጋዴ ለምለም ሆነ እንግዶቿን ለመቀበል ድንቅ ዝግጅት መጀመሯን አረጋግጣለሁ፡፡ ሲል ዳንኤል ሊሬቦ ሶቂዶ
የከተማ ዲዛይን እና ፕላን ተባባሪ ፕሮፈሰር ገልፀዋል።