የሰመራ ከተማ አንደኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሰራ በፍጥነትና ጥራቱን በጠበቀ ደረጃ  ተጠናቆ እውን እንዲሆን ቀን ሌሊት ሳይባል በትጋት በመሠራት ላይ ይገኛል።

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ በክልል ኘሬዚዱንት በክብር
ሀጂ አወል አርባ በሰጡ አቅጣጫ መሠረት በክልላችን ዋና መዲና የሆነችው የሰመራ ከተማ አንደኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሰራ በፍጥነትና ጥራቱን በጠበቀ ደረጃ  ተጠናቆ እውን እንዲሆን ቀን ሌሊት ሳይባል በትጋት በመሠራት ላይ ይገኛል።
ስለሆነም የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች(ቢሮዎች ) እንዲሁም በከተማ ውሰጥ የሚገኙ የመንግስትና የግል ድርጀቶች፣ ሆቴሎች ፣ መኖሪያ ቤቶች የተዘጋጀ የኮሪደር ስታንዳርድ የሕንፃ ውጫዊ ቀለም እና የመብራት ማስዋብ ስራ ከወዲሁ እንዲተገበር መንግሥት አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በዚሁ መሠረት ሁለም ተቋማት ፣ ሆቴሎች ፣ የንግድ ድርጀቶች እና መኖሪያ ቤቶች ከዚህ በታች በምስሉ የተቀመጠውን ስታንዳርድ በመከተልና በመፈፅም የሰመራ ከተማ ውብ፣ ፅዱና ለመኖር ምቹ የሆነች የሠመራ ከተማን እውን ለማድረግ  ለሚደረገው የጋራ ጥረት ላይ ታሪካዊ አሻራ እንድታሳርፋ ሲንል  በአክብሮት ጋር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

➡️የአፋር ክልል ርዕሰ መዲና ሰመራን ውብ፣ ፅዱና ለመኖርያ ምቹ የሆነች ከተማ እናድርግ!!