Uiidp የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የክልሉ Uiidp ፕሮግራም  የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በተዘጋጀ የ8 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ዙርያ ላይ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከባለ ድርሻ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄዱ። የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳም በከተሞች ደረጃ  በተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የተለያዩ የከተማ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በማስመልከትና በከተማ አስተዳደር ደረጃ በገቢ አሰባሰብ ዙርያ ላይ የተሰሩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ሲሆኑ በነኚህ የመወያያ አጀንዳዎች ላይ በውይይት መድረኩ ላይ  ሰፋ ባለ መልኩ ተወያይተዋል። በመቀጠልም መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዬች ላይ በማሻሻል ለቀጣይ ትኩረት በሚሹት ዋና ዋና ጉዳዬች ላይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል በስተመጨረሻም ሴክተር መስሪያ ቤቱም በክልሊ ደረጃ በUiidp ፕሮግራም የተደገፉ የከተማ አስተዳደሮች ለቀጣይ ለሚያከናውኗቸው የጋራ የሆነ የመግባቢያ ሰነዶች ላይ ተፈራርመዋል።