በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለፉት 3 ዓመታት ዙርያ ከ2011 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ የገቢ ማሰባሰብ ዙርያ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀማቸው ምን እንደሚመስል የገመገመ ሲሆን የ2014 እቅድ ላይ በ6 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉና በቀሩት 5 ወራት ውስጥ ሊሰሩ በሚገባቸው ማለትም ለቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው ላይ አቅጣጫ የማስቀመጥ የጋራ የሆነ ውይይት አካሄዱ። በውይይቱ መድረክ ላይ የተገኙትም የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአይሳኢታ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የክልሉ የUiidp ፕሮግራም የሞባይል ቲምና የአይሳኢታ ከተማ የUiidp ፎካል ፐርሰኖች ሲሆኑ ባለፊት 3 ዓመታት ላይ በገቢ አሰባሰብ ዙርያ የተሰሩ ስራዎች ምን ይመስሉ እንደነበርና በ2014 በጀት ዓመቱ በ6 ወራት ውስጥ በአይሳኢታ ከተማ የገቢ አሰባሰብ ዙርያ ላይ የተሰሩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉና እንዲሁም በ2014 በጀት ዓመቱ ማለትም በቀሩት 5 ወራቶች ላይ ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና የገቢ ማሰባሰብያ መስኮቶች ላይ በስፋት ተወያይተዋል። በስተመጨረሻም ለቀጣይ ሊሰሩ በሚገባቸው የገቢ ማሰባሰብ ዙርያ ላይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።