Magaalâ Addah Buqre Taamâ kee Leemat Tu-xiiqi

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት ቢሮ  በሀገር አቀፍ በመካሄድ ላይ ያለው የሌማት ትሩፋቶች እና የከተማ ግብርና መነሻ በማድረግ  በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ የተተከሉትና የምግብነት የደረሱ የጓሮ አትክልቶችን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት የማጨድና የመሰብሰብ ስራ በማካሄድ በቢሮው ደረጃ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ሰራተኞች የመስጠት ፕሮግራም ተካሄደ። በመቀጠልም በቅጥር ውስጥ የተተከሉትን የጓሮ አትክልቶች ከተተከሉ ጀምሮ በቅለው ፍሬ በማፍራት ለምግብነት እንዲውሉ እስኪ ደርሱ ድረስ ደከመኚ ሰለቸኚ ሳይቱ ይንከባከቡና ይሰሩ የነበሩት  የቢሮው አካላት የማበረታቻ ሽልማት ፕሮግራም ተካሄደ። በመቀጠልም የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ።