ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰመራን አዲስ ገጽታ ጎበኙ!

 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሰመራ ከተማን ሁለንተናዊ ገጽታ የቀየሩትን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጎብኝተዋል።

ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ከአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል ዓርባ እንዲሁም ከፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በሠመራ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል።

ከተደረጉት ጉብኝቶች መካከልየ10ኛው የከተሞች ፎረም የተሳተፉት የተለያዩ የከተማ አስተዳደሮችና ሌሎች ኤግዚቢሽን፤  የኮራ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የሰመራ ከተማን ሁለንተናዊ ገጽታ የቀየረው የመጀመሪያ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ የምሽት ድባብ በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎብኝቷል።