ከክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ዑመር ኑር  ጋር   ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሄለን ደበበ በልማታዊ ስራዎች ዙሪያ ተወያዩ።


 

 ከአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ከአቶ ዑመር ኑር  ጋር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሄለን በድሉ  በክልሉ የልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፋ እየተሠሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። 

በውይይቱም  ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች እና የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተው በውይይቱ ተሳትፈዋል።

 ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በበኩላቸው ክልላችንን እንዲሁም ዋና ከተማዋ ሠመራ-ሎጊያን ለኑሮ ምቹ ከተማ እንድትሆን አድርገን አየሰራን ነው ብለዋል። 

   ይህም የክልሉን  ህብረተሰቡ  ከልማት ስራው ሁለንተናዊ  ተጠቃሚ  እንዲሆን ለማድረግ አበክረን እየሰራን ነው ሲሉ  ጠቅሰዎል ።

 ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ከአቶ ዑመር ኑር  በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በሚፈለገው ጊዜ በማጠናቀቅም  የተሻለ አፈፃፀም ሊያሳዩ እንደሚገባም   ለባለድርሻ አካላት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሄለን ደበበ በክልሉ እና በመዲናዋ ሠመራ ከተማ እየተተገበሩ ያሉ የመሠረተ ልማት እና የግንባታ ሂደቶችን አስመልክተው ጥሩ አፈፃፀም አንደተመለከቱ ገልፀው የሚበረታታ ስራ እንደሆነም አመላክተዋል ። 

ሠመራ ከተማ በቀጣይ ለሚካሄደው የከተሞች ፎረም አዘጋጅ እንደመሆኗም ጭምር ከዚህ በላይ የልማት እና የኮንስትራክሽን ስራዎች ሊሠሩ እንደሚገባ ለባለድርሻ አካላት አስገንዝበዋል ።

በመጨረሻም  የባህል አልባሳት  የስጦታ ፕሮግራም ተካሄዶል