"ብክለት ይብቃ! ዉበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ የሚደግ የፅዳት ዘመቻ ጥሪ ..‼️

 

እንደሚታወቀው የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሁሉም የከተማ አስተዳድር አመራሮች እንዲሁም ለክልሉ የመንግስት ሰራተኞችና አጠቃላይ ለከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ባለፉት ቀናቶች ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን "ብክለት ይብቃ! ዉበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል የአፋር ክልል የአከባቢ ብክለትን ለመከላከል ሊተገበር በታቀደው የ6ወራት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የአካባቢ ብክለትን ለመግታት የሚያስችል የንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሩ ይታወቃል። 

በክልለችን ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣዉ የከተማ መስፋፋትና ኃላፊነት የጎደለዉ የፕላስቲክ አጠቃቀም እንዲሁም የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ምክንያት ከተሞች ለሰዎችና ለእንስሳት ለመኖር ምቹ ወደ አለመሆን እንዳይሄዱ ከወዲሁ የአከባቢ ብክለትን መከላከል እንዳለብን በማስታወስ በከተሞች ና በሴክቴር መስረያ ቤቶች   ደረጃም በተጀመረው የአካባቢ ብክለት የመከላከል ዘመቻ ላይ ላደረጋችሁት እንቅስቃሴና በዘመቻው ለተሳተፉት በሙሉ ሴክተር መስሪያ ቤቱ የክብረ ምስጋናውን እያቀረበ የተጀመረው የአካባቢ ማፅዳት ዘመቻ በማስቀጠል ንፁህና እና ፅዱነት ባህላችን ሆኖ እንዲቀጥል በማድረግ የተጀመረውን ዘመቻ ሳንዘናጋና ሳንሰለች መተግበር ይኖርብናል በማለት የክልሉ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

➡️ ኋላ ቀርነትን በመጠየፍ እራሳችንን እናክብር‼️

➡️ የከተሞቻችን ችግርም መፍትሄውም እጃችን ላይ ነው‼️

➡️ የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ውብና ፅዱ ከተሞችን እንፍጠር ‼️