የግል በባለሃብቱ በክልሉ በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ  ጥሪ አቀረቡ 

 


የግል በባለሃብቱ በክልሉ ባለው ሰፊ ለም መሬትና የመአድን ሃብትን ጨምሮ ለወደብ ያለው ቅርበት ምቹ የኢንበቨስትመንት መዳረሻ የሚያደርገው በመሆኑ ኢንቨስት እንዲያደጉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስዳድር ጥሪ አቀረቡ 

ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮቾና ሌሎች ባለድርሻ አካሎች በተገኙበት 10ኛው የከተሞች ፎረም የመክፈቻ መርሃግብር በሰመራ እስታዲየም ተካሂዳል።

በእለቱም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ  የለውጡ መንግስት አፋር ክልልን ጨምሮ ለአርብቶ አደሩ አካባባቢ በሰጠው ልዩ ትኩረት በክልሉ ዘርፈብዙ የልማት ስራዎችን ከማፋጠን ባለፈ ከተሞችን ተወዳዳሪና ለኗሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚስችሉ ሰራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ

ከእነዚህም ውስጥ የ2ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነው የሠመራ ኮሪደር ልማት ስራ 95በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከተማዋን ከጫፍ እስከጫፍ አቋርጦ የሚያልፈው የአሰብ ኮሪደር ልማት ስራም 45 ከመቶ መድረሱን ገልጸዋል

ይህ ከተማችን ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ከማድረግም ባለፈ ኢንቨስትመንት ቱሪዝምን ለማነቃቃትም ባለፈ የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ትራንስፖርት ፍሰት እንዲሳልጥ የማይተካ አይነተኛ ሚና ይጫወታል

ፎረሙም ከከተሞች መካካል ጤናማ  የውድድር መስመር በመፍጠር ለላቀ እድገትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የማይናቅ አስተዋጽኦ  ከማበርከቱም ባሻገር ኢንቨስትመንትን እንደሚያነቃቃም ጠቁመዋል

ከዚህ ባለፈም አፋር ሰፊ ለም መሬትና እምቅ የውሃ ሃብት እንዲሁም የመአድንና ተያያዥ የቱሪዝም ጸጋዎች ያሉት በመሆኑ በዚህ መስክ እየተከናወኑ በሚገኙ ልማት ውስጥ የግል ባለሃብቱ ተሳፎ እንዲያደርግ ጥሪ እያቀረብኩ የክልሉም መግስትም ለግል ባለሃብቱ  አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል እገባለሁ ብለዋል ።